የነዳጅ አቅርቦት ውል ተፈረመ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የሚያቀርበው ነዳጅ ከፊሉን መንግስት ለመንግስት የኢኮኖሚ ትብብር ከነዳጅ አምራች አገሮች የሚገዛ ሲሆን ከፊሉን ደግሞ በዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ አቅራቢዎችን በማወዳደር የድርጅቱን መስፈርት አሟልቶ የተሻለ ዋጋ ካቀረበው ጋር ውል እየገባ የሚያቀርብ መሆኑን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እስመለዓለም ምህረቱ ገልጸዋል።

የቪቶል ባህሬን ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ኬይራን ጋለሄር በፊርማ ሥነሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት ባለፈው ዓመት ድርጅቱ ያወጣውን ዓለም አቀፍ ጨረታ ተወዳድረው በማሸፍ ነዳጅ በማቅረብ ከድርጅቱ ጋር አብሮ በመስራት ኃላፊነቱን መወጣቱን በመግለጽ፤ ይህንንም  አቅርቦት በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በዚሁ መሠረት የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከቪቶል ባህሬን ነዳጅ አቅራቢ ኩባንያ ጋር የ2017 ዓ.ም የነዳጅ ግዥው ውል በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ተፈርሟል።

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic
Scroll to Top
Scroll to Top