ችግኝ ተከላ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከልደታክ/ከተማ ጋር በመተባበር  መኮንኖች ክበብ አከባቢ ሀምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም የችግኝ ተከላ አካሄደ።

የልደታ ክ/ከተማ ም/ቤት ዋና አፈጉባዔ አቶ ዘሪሁን ሽፈርዳ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ በየዓመቱ ክ/ከተማው ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያደርገው ችግኝ ተከላ ሳይቆራረጥ ለረጅም ዓመታት መቀጠሉን አውስተው በቀጣይ ተከላ ብቻ ሳይሆን እንክብካቤው ላይም በበለጠ እንዲሰራ አሳስበዋል። 

በመቀጠል የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እስመለዓለም ምህረቱ ባስተላለፉት መልዕክት ድርጅቱ የሚያስመጣው ምርት ነዳጅ ሲቃጠል ከባቢ አየር የሚበክል በመሆኑ በየዓመቱ በጀት መድቦ በአገሪቱ በተለያዩ ቦታዎቸ (መናገሻ ሱባ፣ እንጦጦ፣ ቡታጀራ፣ ወዘተ) የችግኝ ተከላ ሲያካሄድ መቆየቱን ገልጸዋል። በሌላ በኩል በአገራችን 40 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል የተቀመጠውን አቅጣጫ ለመወጣት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የበኩሉን ሚና ለመጫወት ስለመሆኑም ጨምረው ገልጸዋል። በማያያዝም ችግኝ መትከል ብቻ በቂ ስላልሆነ እንክብካቤው ላይም ትኩረት መደረግ እንዳለበትና ለዚህም ድርጅቱ አስፈላጊውን ሁሉ በመወጣት ላይ መሆኑን አብራርተዋል። በመጨረሻም ፕሮግራሙን ያዘጋጁ አካላትን አመስግነዋል። 

ኮሎኔል ፍሬወይኒ ኃይሉ በችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት “ከካምፕ ወደ ህዝብ” በሚል መሪ ቃል በችግኝ ተከላው እየተሳተፉ መሆኑን ገልጸዋል።

 

የኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ተወካይ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የችግኝ ተከላ ተከናውኗል

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic
Scroll to Top
Scroll to Top