ድርጅቱ ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ደርጅት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች በመደገፍ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል። መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓም የኢድ አል ፈጥር እና የፋስካ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ለልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ድጋፍ አደረገ።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እስመለዓለም ምህረቱ ድጋፉን ለልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ዋና ሥራ አስፈጻሚ ባስረከቡበት ሥነሥዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ድርጅቱ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ሲረዳ መቆየቱን አስታውሰው ከውስን በጀቱ በመቀነስ ድጋፍ ያደገ መሆኑንና ሁሉም አካላት በሚገኙባቸው አከባቢዎች ድጋፍ የሚሹ ወገኖቻችንን በመርዳትና በመደገፍ ማህበራዊ ሃላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል። በቀጣይም ድርጅቱ በሚገኝበት ወረዳ አቅም በፈቀደ መጠን ድጋፍ የሚሹ ወገኖቻችንን መደገፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ዜጎች ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ በሚሰራ ሥራ ውስጥ የድርሻውን እንደሚወጣ ገልጸዋል።

የድርጅቱ ሰው ሃብትና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሰርካለም ዳምጠው በበኩላቸው 570 ሊትር የምግብ ዘይትና 570 ኪ.ግ ዱቄት ብር 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ)  ወጪ በማድረግ የኢድ አል ፈጥር እና የፋስካ በዓላትን ምክንያት በማድረግ የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ገልጸዋል።

የወረዳ 10 ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በላይ ቆየ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ድርጅቱ ላበረከተላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው፤ ሁሉም ተቋማት ባሉበት አከባቢ የማህበራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ፣ የድርጅቱ ድጋፍ አርአያ እንደሚሆን በመግለጽ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish
Scroll to Top
Scroll to Top