ኢነአድ የፕላቲንዬም ዋንጫ ተሸላሚ ሆነ

ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደዉ የታማኝ ግብር ከፋዮች የእዉቅናና ሽልማት ሥነ-ሥረዓት ላይ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የ2015 በጀት ዓመት ከፍተኛ ግብር በመክፈል የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ በመሆኑ ኩራት ይሰማዋል፡፡

በዚሁ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የድርጅቱ የቀድሞው ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ኃይለማርያም ድርጅታችን ለሀገሪቱ ከፍተኛ ግብር በታማኝነት እና በሀቀኝነት በመክፈሉ የፕላቲኒየም ደረጃ እዉቅና የተሰጠው መሆኑን በመግለጽ፣ በቀጣይም ይህንኑ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በዕለቱ ለአዲሱ የድርጅቱ ተ/ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለአቶ እስመለዓለም ምሕረቱ የተሰጠውን የዋንጫ ሽልማት አስረክበዋል፡፡

የድርጅቱ ተ/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እስመለዓለም ምህረቱ ዋንጫውን ሲረከቡ እንደተናገሩት በተገኘው ሽልማት መደሰታቸውንና በሁሉም የማኔጅመንት አባላትና በመላው ሠራተኛ የሥራ ውጤት የተገኘ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ አክለውም የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለሀገራችን ልማት የሚያስፈልጋትን ነዳጅ በማቅረብ እንዲሁም የሚጠበቅበትን ግብር በወቅቱ በታማኝነት በመክፈል የአገር ልማት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish
Scroll to Top
Scroll to Top