ድርጅቱ ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በተለያዩ ጊዜያት ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል። በዚሁ መሰረት ታህሳስ 25 ቀን 2016 ዓ.ም የምግብ ዘይትና ዱቄት ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ ሌሎች የወረዳው ሥራ አመራር በተገኙበት አስረክቧል።
የሰው ሀብትና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሰርካለም ዳምጠው እንደተናገሩት 213 ሊትር የምግብ ዘይት እና 355 ኪ.ግ ዱቄት ድጋፍ መደረጉን፣ ለዚህም ከብር 75,000(ሰባ አምስት ሺህ) በላይ ወጪ ሆኗል ብለዋል።
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እስመለዓለም ምህረቱ በስነ-ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ድርጅቱ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ካለው ውስን በጀት እየቀነሰ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን፤ የመረዳዳት ባህላችንን እያጠናከርን እንዲሁም ሁሉም ዜጋ በተሰማራበት የሥራ መስክ ውጤታማ በመሆን አገራችንን ከድህነት ለማውጣት መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል። በመጨረሻም ድርጅታችን አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ለሚያስገነባው የነዳጅ ማደያ እና ተያያዥ ህንጻ ግንባታ የወረዳው አመራር እና ሠራተኞች ሙያዊ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ዘይነዲን ሁመር የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 መሬት አስተዳደር ኃላፊ እርዳታውን በተረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ድርጅቱ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የማኅረሰብ አካላት ለሚያደርገው ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ድርጅቱ ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ለልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish
Scroll to Top
Scroll to Top