ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (March 8) ተከበረ

በአሜሪካን ሀገር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1908 ብዛታቸው 15 ሺህ የሚሆኑ ሴቶች  የተሻለ ደመወዝ፣ ጥሩ የሥራ አካባቢና የሥራ ሰዓት ማስተካከያ  እንዲሁም የሴቶች የመምረጥ መብት እንዲከበር ለመጠየቅ ወደ አደባባይ ወጡ፡፡

ሴቶች በአደባባይ ወጥተው ነፃነታቸውን የጠየቁበትን ቀን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት “የሴቶች ቀን ብሎ” በማወጅ ዓለም አቀፍ ይዘት ኖሮት በየዓመቱ እንዲከበር እ.ኤ.አ በ1975 ውሳኔ አስተላለፈ።  ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (March 8) ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ የመጣ ሲሆን ዘንድሮም “Invest in Women accelerate progress” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ “ሴቶችን እናብቃ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል የድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በተገኙበት በተለያዩ መርሐ ግብሮች ተከብሯል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እስመለዓለም ምህረቱ በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዓለማችን እንዲሁም በሀገራችን የሴቶች ትግል ፍሬ አፍርቶ በአሁኑ ጊዜ የሴቶች መብት እየተከበረ ወደ አመራርነት እየመጡ እና ተፅዕኖ እየፈጠሩ እንዳሉ፣ በኢትዮዽያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅትም ከቅጥር ጀምሮ በተለያዩ ደረጃዎች ሴቶች ወደ አመራርነት እንዲመጡ ትኩረት ተሰጥቶበት እየተሰራ ሲሆን  በዚህም እስከ ሥራ አስኪያጅነት ደረጃ መድረሳቸውን ገልጸዋል። የሴቶች መብት እንዲከበር ወንዶችም ኃላፊነት እንዳለባቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸው ድርጅቱ የሴቶች መብት እንዲከበር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የድርሻውን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።

ድርጅቱ የሴቶች ሰራተኞች ህጻናት ማቆያ ገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ህጻናቱን የሚንከባክቡ ወ/ት ሔሌን ታደሰ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ከድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከአቶ እስመለዓለም ምህረቱ ብር 10,000 (አሥር ሺህ) ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ከ13 የነዳጅ ዴፖ ጽ/ቤቶች የሥርዓተ ጾታ ተወካዮች በበዓሉ ላይ የታደሙ ሲሆን የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በመጡ ባለሙያ በአቶ አበበ ኃይማኖት እና በድርጅቱ ሥርዓተ ጾታ ባለሙያ በወ/ሮ መስከረም አሰፋ በዓሉን በማስመልከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish
Scroll to Top
Scroll to Top