ዕለታዊ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ዕለታዊ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ


ቢያስፈለግዎ ቢያስፈለግዎ

አግኙን አግኙን

ዜና ዜና

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 1,005,490 ሜ.ቶን ነዳጅ ቀረበ

በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት(ሐምሌ 30/ 2014-መስከረም 30/2015 በጠቅላላው 1,006,537 ሜ.ቶን ነዲጅ ለመግዛት ታቅዶ 1,005,490 ሜ.ቶን ነዳጅ የተገዛ ሲሆን፣ አፈፃፀሙ 94% ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ለዚህም ከብር 77.85 ቢሊዮን በላይ ወጪ ሆኗል፡፡ የነዳጅ ምርቶች ግዥ አፈጻጸም ዝርዝር በሚከተለው

ተጨማሪ ያንብቡ..

ድርጅቱ በፕላቲኒዬም ደረጃ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ

ድርጅታችን የነዳጅ አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን በመንግሥትና በሕዝብ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ግብር የመክፈል ግዴታውን በብቃት ስለተወጣ በግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ዕውቅና ሲሰጠው ይህ በተከታታይ ለሶስተኛ ጊዜ ነው፡፡ ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ/ም በግብር ሰብሳቢው መ/ቤት በተዘጋጀ መርሃ ግብር ላይ በ2014 በጀት ዓመት ከብር 3.9 ቢሊዮን በላይ ታክስ በመክፈሉ የፕላቲኒዬም ደረጃ

ተጨማሪ ያንብቡ..

በ2014 በጀት ዓመት ከ3.85 ሚሊዮን ሜ.ቶ በላይ ነዳጅ ቀረበ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በ2014 በጀት ዓመት በ12 ወራት (ሀምሌ 2013 እስከ ሰኔ 2014) በጥቅሉ 4,167,486 ሜ.ቶን የተጣራ የነዳጅ ምርቶችን ለማቅረብ ታቅዶ 3,849,181.703 ሜ.ቶን

ተጨማሪ ያንብቡ..

ከ2.88 ሚሊዮን ሜቶን በላይ ነዳጅ ቀረበ

በ2014 በጀት ዓመት በ9 ወራት (ሀምሌ 2013 እስከ መጋቢት 2014) በጥቅሉ 3,103,288 ሜ.ቶን የተጣራ የነዳጅ ምርቶችን ለማቅረብ ታቅዶ 2,885,270 ሜ.ቶን ነዳጅ ቀርቧል፡፡ የዕቅድ እና ክንውን አፈጻጸም

ተጨማሪ ያንብቡ..

በ2014 መጀመሪያው ስድስት ወራት 1,941,765 ሜ.ቶን ነዳጅ ቀረበ

በ2014 በጀት ዓመት 6 ወራት (ሀምሌ 2013 እስከ ታህሳስ 2014) በጥቅሉ 2,043,605 ሜ.ቶን የተጣራ የነዳጅ ምርቶችን ለማቅረብ ታቅዶ 1,941,765 ሜ.ቶን ነዳጅ ቀርቧል፡፡ ዕቅድ እና ክንውን ንጽጽር 95

ተጨማሪ ያንብቡ..

የዋና ሥራ አስፈጻሚው መልዕክት

ስለድርጅታችን ወቅታዊና ተጨባጭ መረጃ የሚሰጣችሁን የድርጅታችን ድረገጽ ስለጎበኛችሁ በኢትዮጰያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አመራርና ሰራተኞች ስም እንኳን ደህና መጣችሁ እላለሁ፤ አመሰግናለሁ፡፡ ድርጅታችን መንግስታዊ የልማት ድርጅት ሲሆን፤ የተጣራ ነዳጅ ከውጭ ሀገር ገዝቶ በማስገባት ለመላ ሀገሪቱ የሚያስፈልገውን ነዳጅ ላለፉት 56 ዓመታት ሲያቀርብ የቆየና በማቅረብ ላይ ያለ ብቸኛ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ነው ፡፡

ድርጅቱ በተለያዩ ጊዜያት የተለያየ ስያሜ እና አደረጃጀት እየያዘ ነዳጅ በማቅረብ ስራ ላይ ተሰማርቶ የቆየ አንጋፋ ድርጅት ሲሆን፤ ለሃገሪቱ የሚያስፈልገውን በቂ ነዳጅ ከማቅረብ ባሻገር በየጊዜው የነዳጅ ተደራሽነት እንዲሰፋ የበኩሉን ጥረት ሲያደርግ የቆየ ድርጅት ነው፡፡

ከነዳጅ ተደራሽነት በተጨማሪ የህዝቡንና የደንበኞችን የመረጃ ፍላጎት ለማርካት የመረጃ ተደራሽነትም ተገቢው ትኩረት የሚያስፈልገው በመሆኑ የወቅቱን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘዴና መሳሪያዎች በመጠቀም አሰራሩን በማዘመን ላይ ይገኛል ፡፡

ድርጅቱ ከዘረጋቸው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መገናኛ ዘዴዎች መካከል ይህ ድረገጽ አንዱ ሲሆን፤ እርሰዎ ጊዜ ሰጥተው ድረገጻችን ስለጎበኙ በድርጅታችን  ስም እያመሰገንኩ እርሶዎም ሆኑ ስለድርጅታችን ማወቅ፣ ድጋፍና አስተያየት መስጠት እንዲሁም ሃሳብና ግብረመልስ መስጠት የሚፈልጉ ሌሎች በመላው አለም የሚገኙ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች በየጊዜው ድረገጻችንን በመጎብኘት መረጃ የማግኘት ፍላጎትዎን እንዲያሟሉ፤ አስተያየትም እንዲሰጡ እጋብዛለሁ፡፡ ለማገልገልና ለመማር ሁሌም ዝግጁ ነን::